logo

Enem Le hagere Youth association

addis ababa, Ethiopia
Joined September 2020

እኔም ለሀገሬ ህብረት ኢትዮጵያዊያንን ወደ ኢትዮጵያዊነት ለመመለስ አላማው አድርጎ የተነሳ ህብረት ነው። ኢትዮጵያዊያንን ወደ ኢትዮጵያዊነት መመለስ ማለት በአሁኑ ጊዜ ካለው የምዕራባውያንነት አስተሳሰብ ትውልዱን ወደ ሀገራችን ባህል ፣ እሴቶችና ጥበቦቻችን ዳግም መመለስ ማለት ነው።Presence in: Ethiopia
Focus: Citizenship & Identification, Community / Customary Land Rights, Education, Family, Traditional / Customary Justice

ባለ ትልቅ ህልም ‘እኔም ለሀገሬ’ ህብረታችን ከተመሰረተ ወራት ተቆጥረዋል እኔ፣ አንቺ፣ አንተ፣ እናንተ፣ ሁላችንም ለሃገራችን ለመስራት አለሁ ብለን ከተሰባሰብን ቀናት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን ተክተው እነሆ ዛሬ ላይ ደርሰናል በነዚህ ጊዚያትም የምንችለውን ያህል ስለ ሀገራችን ብለን ተንቀሳቅሰናል ወጣቱ ማንነቱን የተረዳ ንቁ ትውልድ እንዲሆን ስንጥር ቆይተናል፤ ለዚህም የተለያዩ ሀገርኛ ቻናሎችን በማብዛት ስለ ሀገራችን ታሪክና ጥበብ የሚያሳውቁን የሚያነቁ ድምፆችን በየ ማህበራዊ ሚዲያው ስናሰማ ቆይተናል።

እንግዲህ ‘እኔም ለሀገሬ’ ብለን መሰባሰባችን የመጨረሻ ግቡ ነገ ሀገራችን የጥበበኞች ሀገር ነበረች ሳይሆን የጥበበኞች ሀገር ነች፣ የአማኞች ሀገር ነበረች ሳይሆን የአማኞች ሀገር ነች፣ የአለም ተምሳሌት ነበረች ሳይሆን የአለም ተምሳሌት ነች፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የመከባበር፣ የአንድነት፣ የፍትህ ሀገር ነበረች ሳይሆን አሁንም ነች የሚባልበትን ቀን ለመስማት ለመኖርም ጭምር ነው
ደግሞም እንችላለን፤ ለዚህ ግባችን መሳካት ይረዳን ዘንድ ልንሰራበት ያሰብነው አላማዋቻችን በለን የስቀመጥነውን ዝርዝር እነሆ እንደሚከተለው ብለናል የህብረታችን አላማ ነጥቦች እንመልከት
አላማችን በሁለት መንገድ ያስቀመጥን ሲሆን የመጀመሪያው ገና ከመሰረቱ (ህፃናቱ)ላይ ያተኮረ ነው ይህም
፩ኛ. ህፃናቶቻችን በንፁህ ወረቀትነት እድሜያቸው ስለ እውነተኛ ማንነታቸው የተገነዘቡ እንዲሆኑ ማስቻል (በየአካባቢያችን ካሉ ህፃናት ጀምረን ማስተማር )
፪ኛ.ህፃናቱን ከሚያታልሉ በምግባር ከሚገድሉ የምዕራባዊያን ተፅዕኖ የተጠበቁ ነገ ላይ ማንነታቸውን የተገነዘቡ ሁነው እንዲገኙ ማስቻል (በየትምህርት ቤቶቻቸው የሚማሯቸውን ትምህርቶች ጭምር መመርመር)
፫ኛ. መጭው ትውልድ ከአስተዳደጉ ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅንና በተግባርም የሚኖረው እንዲሆን ማስቻል (ዘወትር ስለማንነቱ በማስረዳትና ሀገሩን በመውደድ እንዲያድግ በመስራት)

ሁምዕራባዊያኑ የራሳቸውን ልጆች አሰለጠንን ብለው አሰይጥነው ጨርሰዋል ዛሬ ደግሞ አይኖቻቸው የኛ ወጣቶች ላይ ነውና ወጣቶች ላይ መስራቱ አስፈላጊ በመሆኑ ከታች በተዘረዘሩት አበይት አላማዋች የምንንቀሳቀስ ይሆናል።

፩. ከተባበርን ሁሉን እንችላለንና አንድ ላይ ሰርተን ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ስሜት ያደረበት የወጣቶችን ቁጥር ማብዛት ዋናውና ትልቁ አላማው ነው
፪. ወጣቶች ለአንዲት ሀገር ህልውና በምንም የማይተካ ሚና እንዳላቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነውና የሀገራችን 70%ና ከዛም በላይ የሚሆነው ወጣት በፖለቲካ ሽፋን እና በምዕራባዊያን ተፅዕኖ ከሚመጣ ችግር የተጠበቀ፤ በሀገራችን ከመጣው ትልቅ ፈተና በተቻለ መጠን መረጃ በመለዋወጥ እራሱን ጠብቆ ሀገሩንም መጠበቅ የሚችል እንዲሆን ማስቻል
፫. ይህንን ወጣት ሃይል በአሁኑ ጊዜ በውስጡ ያደረበትን የዘረኝነት መንፈስ በመንቀል ኢትዮጵያዊነት ብቻ በደሙ የሚንሸራሸርበት ሀገራችን ከነክብሯ ለቀጣይ ማስተላለፍ የሚችል ለማንነቱ ክብር የሚሰጥ ወጣት እንዲፈጠር ማስቻል።
፬.የቀደመ ስልጣኔዎቻችን፣የተከፈለልንን መስዕዋትነት እና ከአባቶቻችን የተቀበልነውን ጥበባቶች አደራዋች በማስታወስ ሀላፊነት የሚሰማው ንቁ ኢትዮጵያዊ ወጣት ማብዛት